አገልግሎቱ ያስገነባው የአረጋውያንና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ብሎክ በክቡር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በይፋ ተመረቀ
አገልግሎቱ ያስገነባው የአረጋውያንና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ብሎክ በክቡር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በይፋ ተመረቀ
ዜና፣ አዲስ አበባ፣ ሰኔ 09 ቀን 2018 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የመንግስት ግዥ አገልግሎት ከተቋቋመበት ዋና ዓላማ ጎን ለጎን፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገውን የበጎ አድራጎት ተሳትፎ አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህም መሰረት አገልግሎቱ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ያስገነባው የስድስት ቤተሰብ የአረጋውያንና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ሁለት ብሎኮችን በገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እና በመንግስት ግዥ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል፡፡
የመኖሪያ ብሎኮችን በክብር እንግድነት ተገኝተው የመረቁት የገንዘብ ሚኒስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የመንግስት ግዥ አገልግሎት ለወገኖቹ ያደረገውን ድጋፍ አድንቀዋል።