አገልግሎቱ ለቋሚ ኮሚቴው የግንዛቤ ማስጨበጫ የስልጠና መድረክ አካሄደ
አገልግሎቱ ለቋሚ ኮሚቴው የግንዛቤ ማስጨበጫ የስልጠና መድረክ አካሄደ
ዜና፡ አዳማ፣ ታህሳስ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በማዕከል ግዥ እና ንብረት ማስወገድ የህግ ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ የስልጠና መድረክ አካሂዷል፡፡
በመድረኩም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጆ፣ ም/ሰብሳቢው የተከበሩ ዶ/ር አብርሃም አለማየሁ እና የቋሚ ኮሚቴው አባላትን ጨምሮ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ እና ሌሎች የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ስራ አሰፈፃሚዎች እና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ እንዳሉት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን ማካሄድ ያስፈለገበት ዋና ዓላማ ቋሚ ኮሚቴው የአገልግሎቱን ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ በመያዝ አስፈላጊውን ድጋፍ እና እገዛ ማድረግ እንዲያስችለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመቀጠል የአገልግሎቱ ግዥ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ወርቁ ገዛኸኝ በማዕከል ግዥ እና ንብረት ማስወገድ የህግ ማዕቀፍ እና የአሰራር ሰነዶች ላይ በዋናነት የግዥ ዘዴዎች፣ የግዥ ስልቶች፣ በግዥ ዙሪያ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣ የመንግስት ግዥ አገልግሎት እና ተጠቃሚ የመንግስት መ/ቤቶች ተግባርና ኃላፊነት፣ ንብረትን በሽያጭ ማስወገድ እና የማስወገጃ ዘዴዎች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና አገልግሎቱ ከቋሚ ኮሚቴው የሚፈልጋቸው መሰረታዊ ድጋፎች በሚሉ ነጥቦች ላይ ትኩረት በማድረግ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ከቀረበው ገለፃ በመነሳትም ከቋሚ ኮሚቴ አባላት አስተያየትና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በዋናነት የቴክኒክ ፍላጎት መገለጫ ዝግጅት ላይ፣ የተቋማት የግዥ እቅድ በወቅቱ እንዲያቅዱ ክትትል ማድረግ ላይ፣ አገልግሎቱ ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ጋር በቅንጅት መስራት ላይ፣ የርክክብ እና ክፍያ ሁኔታ፣ የውል አስተዳደር ላይ፣ ለተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መፍጠር ላይ፣ የአገልግሎቱን ማቋቋሚያ ደንብ ማሻሻል ላይ፣ በመንግስት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ (e-GP) ስርዓት ዙሪያ እና ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠርና ሰራተኛ ተረጋግቶ እንዲቆይ ማድረግ ላይ ጥያቄና አስተያየቶች ተነስተው በበላይ አመራሮችና በሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተስጥቷል፡፡
በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ መድረኩን በማስመልከት አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን አገልግሎቱ በመንግስት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ (e-GP) ስርዓት እየፈጸመ ያለው ግዥ ጥሩ እና ከሙስናና ብልሹ አሰራር የሚታደግ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት፣ ተቋማት የግዥ እቅዳቸውን በወቅቱ አቅደው እንዲልኩ ክትትል ማድረግ እና በወቅቱ አቅደው የማይልኩ ተቋማት ግዥ መፈጸም እንደማይችሉ ተገቢውን ግንዛቤ መፍጠር፣ በንብረት ማስወገድ ዙሪያ ተቋማት ድረስ በመሄድ ንብረታቸውን እንዲያስወግዱ የተደረገው ድጋፍና ክትትል አበረታች እንደሆነ፤ ሆኖም አሁንም በየቦታው መወገድ የሚገባው በርካታ የንብረት ክምችት ያለ በመሆኑ አገልግሎቱ ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት አልፎ ንብረቶችን ለማስወገድ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት፣ በአገልግሎቱ ዋና ዋና ስራዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለተቋማት መስጠት ላይ ትከረት ተደርጎ መሰራት እንዳለበት፣ አገልግሎቱ ተመሳሳይ ተቋማት ላይ ጥናት በማድረግ የሰራተኞችን ደመወዝ እንዲስተካከል እና ጥቅማጥቅም እንዲኖር በማድረግ የሰራተኞችን ፍልሰት መቀነስ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ እና አገልግሎቱ እየሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን በመግለጽ አሁን እየሰራበት ያለውን አሰራሩን ግልጽ፣ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ ማድረግ ላይ ያለመስልቸት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በማመላከት የውይይት መድረኩን አጠቃለዋል፡፡
The Service Conducted an Awareness-Raising Training Forum for the Standing Committee
News: Adama, Tahisas 26, 2018 E.C.
The Public Procurement Service conducted an awareness-raising training forum focused on the legal frameworks of centralized procurement and property disposal for members of the Standing Committee on Plan, Budget, and Finance Affairs of the House of Peoples’ Representatives of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (FDRE).
The forum was attended by the Chairperson of the Standing Committee, H.E. Mr. Desalegn Wodajo; the Vice Chairperson, H.E. Dr. Abraham Alemayehu; members of the Standing Committee; the Director General of the Service, H.E. Mr. Asmare Yigezu; as well as other senior officials, executives, and relevant experts of the Service.
In his opening and welcoming remarks, the Director General of the Service, H.E. Mr. Asmare Yigezu, stated that the main purpose of organizing the awareness-raising forum was to enable the Standing Committee to gain a clear understanding of the Service’s mandate, roles, responsibilities, and the services it provides, thereby allowing the Committee to offer the necessary support and assistance.
Following this, the Service’s Deputy Director General for Procurement, Mr. Werku Gezahagn, delivered a presentation focusing on the legal framework and procedural documents governing centralized procurement and property disposal. His presentation covered procurement methods and strategies; the roles and responsibilities of the Public Procurement and Property Authority, the Public Procurement Service, and beneficiary public institutions; property disposal through sale and other disposal methods; challenges encountered; and the key areas of support required from the Standing Committee.
Based on the presentation, members of the Standing Committee raised questions and provided comments. These focused mainly on the preparation of technical specifications; monitoring institutions to ensure timely procurement planning; coordination between the Service and the Public Procurement and Property Authority; delivery and payment conditions; contract management; creating awareness-raising platforms for institutions; revising the Service’s establishment regulation; the government electronic procurement (e-GP) system; and creating a conducive working environment to ensure staff stability and retention. Responses and clarifications were provided by senior management and relevant officials.
In closing, the Chairperson of the Standing Committee, H.E. Mr. Desalegn Wodaje, delivered concluding remarks. He noted that procurement activities being carried out through the government electronic procurement (e-GP) system are commendable and help prevent corruption and malpractice, and therefore should be strengthened and continued. He emphasized the need to closely monitor institutions to ensure that they prepare and submit their procurement plans on time, and to create proper awareness that institutions failing to do so will not be able to conduct procurement.
He further stated that the support and follow-up provided by the Service to institutions to facilitate property disposal is encouraging; however, since there remains a significant amount of property awaiting disposal in various locations, the Service should continue strengthening its efforts beyond its assigned duties. He also stressed the importance of providing awareness-raising support to institutions on the Service’s core functions.
Additionally, he recommended that the Service conduct comparative studies with similar institutions to improve staff salaries and benefits in order to reduce employee turnover. He concluded by stating that the work being carried out by the Service is encouraging and emphasized the need to continue strengthening its operations to make them transparent, efficient, and modern, thereby formally closing the discussion forum.