ቋሚ ኮሚቴው በአገልግሎቱ በመገኘት ሱፐርቪዥን በማድረግ ውይይት እና የቢሮ ምልከታ አካሄደ
ቋሚ ኮሚቴው በአገልግሎቱ በመገኘት ሱፐርቪዥን በማድረግ ውይይት እና የቢሮ ምልከታ አካሄደ
ዜና፡ አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በመንግስት ግዥ አገልግሎት መ/ቤት በመገኘት ሱፐርቪዥን አካሂዷል፤ የቢሮ ምልከታም አድርጓል፡
በውይይቱም የቋሚ ኮሚቴው ም/ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር አብርሃም አለማየሁ እና የቋሚ ኮሚቴው አባላት እንዲሁም የአገልግሎቱን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙን ጨምሮ የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተሮችና የሚመለከታቸው የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በ2017 በጀት ዓመት እና ባለፉት ስድስት ወራት የተሰሩ አበይት ስራዎች ሪፖርት ለቋሚው ኮሚቴ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን፤ በዋናነት አገልግሎቱ የአሰራር ስርዓቱን በማዘመን የማዕቀፍ ስምምነት እና ስትራቴጅክ ግዥዎችን ሙሉ በሙሉ በመንግስት የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ስርዓት (e-GP) ሲስተም መፈፀሙን፤ የንብረት ማስወገድ እና የውል አስተዳደር ስራዎችን በዚሁ ሲስተም ለመፈጸም ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግር ተደርገው ሲወሰዱ የነበሩ ለረዥም ጊዜ ሳይዘጉ የነበሩ በርካታ ውሎች መዘጋታቸውም ተገልጾላቸዋል፡፡
እንዲሁም አገልግሎቱ አሰራሩን ዲጂታላይዝ በማድረግ የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን በዋናነት ተግባራዊ ከተደረጉ የዲጂታል ስራዎች መካከል የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ስርዓት (e-GP)፣ የነዳጅና ተሽከርካሪ ስምሪት አስተዳደር (e-fleet management system)፣ የICMIS፣ የIFMIS እንዲሁም e-payment እና የ5 ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠናና ሌሎች በርካታ ስራዎችም መሰራታቸው በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም አገልግሎቱ የሪፎርም የትግበራ ምዕራፍ ላይ መሆኑን በዚህም ለሪፎርሙ ማስፈጸሚያ የተለያዩ ሰነዶች መዘጋጀታቸው ተገልጾላቸዋል፡፡
በቀረበው ሪፖርት እና የቢሮ ምልከታ መነሻ ከቋሚ ኮሚቴው ለተነሱ አስተያየት እና ጥያቄዎች በአገልግሎቱ የበላይ አመራሮች ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ከቀረበው ሪፖርት እና ካደረጉት የቢሮ ምልከታ በኋላ በሰጡት ግብረ መልስ አገልግሎቱ እያደረገ ያለው የተቋም ግንባታ አበረታችና የሚታይ መሆኑን፤ ጥራትና ቅልጥፍናን የተቋሙ ባህል ለማድረግ እያከናወነው የሚገኘውን የዲጂታላይዚሽን ስራ እንዲሁም በማህበራዊ አገልግሎት ተሳትፎ ላይ እያከናወነ ያለው ተግባር የሚበረታታ ነው በማለት አድናቆታቸውን የገለጹ ሲሆን በውስንነት የታዩ ተግባራት ላይም ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበትም በማመላከት የቋሚው ኮሚቴ የሱፐርቪዥን ስራ ተጠናቋል።
The Standing Committee Conducted Supervision, Discussions, and Office Inspection by Visiting the Institution
News: Addis Ababa, Tahsas 16, 2018 E.C.
On this day, the Standing Committee on Planning, Budget, and Finance Affairs of the House of Peoples’ Representatives of the Federal Democratic Republic of Ethiopia conducted a supervision visit to the Public Procurement Service. The Committee also carried out discussions and an office inspection.
The discussion was attended by the Vice Chairperson of the Standing Committee, the Honorable Dr. Abraham Alemayehu, members of the Standing Committee, the Director General of the Service, His Excellency Mr. Asmare Yigezu, Deputy Directors General, and relevant senior officials of the Service.
A detailed report on major activities carried out during the 2017 budget year and the past six months was presented to the Standing Committee. The report highlighted that the Service has modernized its operational systems and fully implemented framework agreements and strategic procurements through the Government Electronic Procurement System (e-GP). It was also reported that extensive work is underway to execute asset disposal and contract administration through the same system. In addition, the report indicated that numerous long-outstanding contracts, previously considered governance challenges, have now been successfully closed.
Furthermore, detailed information was presented on activities implemented through the digitalization of the Service’s operations. Key digital initiatives already implemented include the Government Electronic Procurement System (e-GP), Fuel and Vehicle Fleet Management System (e-fleet management system), ICMIS, IFMIS, e-payment systems, the Five Million Ethio Coders training program, and several other initiatives, as indicated in the report.
It was also explained that the Service is currently in the implementation phase of reform, and that various documents have been prepared to support the execution of these reforms.
Based on the presented report and the office inspection, senior management of the Service provided explanations and responses to comments and questions raised by members of the Standing Committee.
Finally, following their review of the report and the office inspection, members of the Standing Committee expressed their feedback, noting that the institutional capacity-building efforts being undertaken by the Service are encouraging and visibly effective. They commended the ongoing digitalization efforts aimed at making quality and efficiency part of the institution’s culture, as well as the Service’s engagement in social responsibility activities. At the same time, they emphasized the need to give due attention to areas where limitations were observed.
With this, the Standing Committee’s supervision activity was concluded.